FAQs ( አማርኛ)
የቻርተር ምርመራዎች እምቅ ውጤቶች ምን ሊሆኑ ይችላሉ?
DC PCSB ትምህርት ቤቶችን በየአምስት አመት ይመረምራል (ለምሳሌ፣ 5ኛ፣ 10ኛ ፣ 20ኛ፣ 25ኛ)። የቻርተር ምርመራ ሪፖርቱን ከተመረመረ በኋላ፣ የDC PCSB የትምህርት ቤቱን ቻርተር መቀጠል ወይም መሰረዝ ያለበት ስለመሆኑ መምረጡን ይቀጥላል። የትምህርት ቤት ህግ ወይም SRA ይህን ውሳኔ በተመለከተ ለDC PCSB የተወሰነ ስልጣን ይፈቅድለታል፣ ቦርዱ ትምህርት ቤቱ ግቦቹን በሙሉ እንዳላሳካ ካሰበ፣ ወይም ትምህርት ቤት ጉልህ የህግ ጥሰት ከፈጸመ፣ የትምህርት ቤቱን ቻርተር ለመሰረዝ ወይም ከዚያ ይልቅ ቻርተሩ እንዲቀጥል(በሁኔታዎች ወይም ከሁኔታዎች ውጪ) ሊመርጥ ይችላል።
ነገር ግን፣ ቦርዱ ትምህርት ቤቱ ጉልህ የሆነ የገንዘብ እጥረት እንዳለው ካወቀ (በተለይም፣ ትምህርት ቤቱ ፣ (1) አጠቃላይ ተቀባይነት ያላቸውን የአካውንቲንግ መርሆችን አልተከተለም፣ (2)በተደጋጋሚ ተገቢ ያልሆነ የበጀት አስተዳደር ላይ ተሳትፏል፣ ወይም (3) ኢኮኖሚካሊ አዋጭ አይደለም)፣ ቦርዱ የትምህርት ቤቱን ቻርተር እንዲሰርዝ ይጠበቃል።
ከቻርተር ምርመራ በፊት አንድ ትምህርት ቤት ቻርተሩን ሊያሻሽል ይችላል፣ በተልይም ግቦቹን እና የሚጠበቁ ውጤቶቹን ?
ምንም እንኳን አንድ ትምህርት ቤት ቻርተሩን ለማሻሻል ጥያቄውን በማናቸውም ጊዜ ማቅረብ ቢችልም፣ DC PCSB ከትምርት ቤቱ 13ኛ ወይም 15ኛ የስራ አመት በፊት ከሁለት አመታት አስቀድሞ ወይም የትምህርት ቤቱ አምስተኛ፣ 10ኛ፣ 20ኛ ወይም 25ኛ የስራ አመት ምርመራ አንድ አመት በላይ ቀደም ብሎ ካልሆነ፣ከሚደረግ የቻርተር ማሻሻያ ጥያቄ ካልሆነ በስተቀር የትምህርት ቤት ግቦች እና የሚጠበቁ ውጤቶችን አስመልክቶ ማሻሻያዎችን በአጠቃላይ አያጸድቅም። ለዚህ ልዩ ተቀባይነት ያለው ምክንያት ትምህርት ቤቱ የአፈጻጸም አስተዳደር ማእቀፍን ወይም PMF የቻርተሩ ግቦች እና የሚጠበቅ የአካዳሚክ ስኬት አድርጎ ለማካተት ከመረጠ ነው። PMF እንደ ግቦች የመምረጥ ፖሊሲ መሰረት (ፖሊሲን ይመልከቱ እዚህ፣ DC PCSB ክለሳውን ከትምርት ቤቱ 13ኛ ወይም 15ኛ የስራ አመት በሁለት አመታት ውስጥ ወይም በቻርተር ትምህርት ቤት ምርመራ በአንድ አመት ውስጥ እንዲደረግ ሊፈቅድ ይችላል። ፖሊሲው ይመልከቱ እዚህ ። የቻርተር ማሻሻያ ጥያቄ ለማዘጋጀት መመርያዎች እዚህ ይገኛሉ።
የቻርተር እድሳት ምንድን ነው?
እያንዳንዱ የ DC የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤት የ15- አመት የቻርተር ስምምነት ያገኛል። አንድ ትምህርት ቤት ከእነዚህ 15 አመታት በላይ መስራት መቀጠል ከፈለገ፣ በትምህርት ቤት ማሻሻያ ህግ፣ ወይም በ SRA ፣ መሰረት ለሌ የ15- አመት ክፍለጊዜ ቻርተሩን ለማደስ ለ DC PCSB ማመልከቻ እንዲያስገባ ይጠበቃል። በተለዋጩ፣ ቦርዱ በትምህር ቤት ማሻሻያ ህጉ ወይም SRA መሰረት ትምህርት ቤቱ የሚከተሉትን ማድረጉን ካወቀ የትምህርት ቤቱን ቻርተር እንዳያድስ ይጠበቃል፣
-
አግባብነት ያላቸውን ጉልህ ህጎች ( የልዩ ትምህርት ህጎችን ጨምሮ) ወይም የቻርተሩን የስምምነት ቃሎችን፣ ሁኔታዎችን፣ መስፈርቶችን፣ ወይም ስነ ስርአቶቹን ከጣሰ።
-
ግቦቹን እና የተማሪ የሚጠበቅ የአካዳሚክ ስኬት ማሟላት ካልቻለ።
-
አጠቃላይ ተቀባይነት ያላቸውን የአካውንቲንግ መርሆችን ካልተገበረ፣ የተደጋገመ ተገቢ ያልሆነ የበጀት አስተዳደር፣ እና/ወይም ኢኮኖሚካሊ አዋጭ ካልሆነ።
የቻርተር ምርመራ ሂደቱን በተመለከተ ለተጨማሪ ጥያቄዎች፣ ያግኙ Nikhil Vashee
nvashee@dcpcsb.org ።
የቻርተር ምርምራ ምንድን ነው?
የቻርተር ምርመራ በትምህርት ቤት ማሻሻያ ህግ(SRA) የሚጠየቅ የትምህርት ቤቱ የአካዳሚክ አፈጻጸም፣ የህግ ማክበር፣ እና የበጀት አስተዳደር ምዘና ነው። የ DC የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤት ቦርድ (DC PCSB) በእነዚህ ስፍራዎች ላይ ያለውን ምዘና የሚዘረዝር የምርመራ ሪፖርት ያዘጋጃል፣ የቻርተሩ ምርመራ የሚያበቃው ቦርዱ የትምህርት ቤቱን ቻርተር መቀጠል ወይም ደግሞ መሰረዝ እንዳለበት በመምረጥ ነው። እነዚህ የቻርተር ምርመራዎች በእያንዳንዱ ትምህርት ቤት አምስተኛ እና 10ኛ የስራ አመት ላይ የሚከናወኑ ናቸው።
የትምህርት ቤቶችን የቀድሞ የምርመራ ሪፖርቶችን እዚህ ይመልከቱ።
የኔ ትምህርት ቤት የቻርተር ምርመራ እንዲያደርግ ለምን አስፈለገ?
DC PCSB በትምህርት ቤት ማሻሻያ ህግ ወይም SRA መሰረት እያንዳንዱን ትምህርት ቤት በየአምስት አመት ቢያንስ አንድ ጊዜ እንዲመረምር ይጠበቃል። በአጠቃላይ፣ እነዚህ የቻርተር ምርመራዎች የሚከናወኑት በእያንዳንዱ ትምህርት ቤት አምስተኛ እና አስረኛ አመት የስራ ጊዜ ላይ ነው፣ እና አስፈላጊ ከሆነ፣ ከዚህ የጊዜ ሰሌዳ ውጭ ተጨማሪ ምርመራዎችን እናደርጋለን።
እኛ የቻርተር ምርመራ ልናከናውን እንችላለን ትምህርት ቤቱ የሚከተለው ከሆነ፣
-
ውጤቶችን ለማስላት የአፈጻጸም አስተዳደር ማእቀፍ (PMF) በሚጠቀመው በትምህርት ቤት ጥራት ሪፖርት ላይ በእርከን 3 ላይ ተለይቷል።
-
አስቀድሞ የነበረውን የቻርተር ምርመራዎች እና የእድሳቶች ሁኔታዎቹን እያሟላ አይደለም
በ DCPS አስተማሪ ደሞዞች እና በህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤት አስተማሪ ደሞዞች መካከል ልዩነቶች አሉ?
የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤቶች የሰራተኛን ደሞዝ ጨምሮ፣ ሰራተኞቻቸውን በተመለከተ ሙሉ ስልጣን አላቸው። ነገር ግን፣ እኛ በየትምህርት ቤቱ አጭር ታሪክ ገጽ ላይ ከፍተኛ ተከፋይ የሆነውን ሰራተኛ መረጃን እናካትታለን። የአጭር ታሪክ ገጾችን እዚህ ይመልከቱ
በ CMO እና በገለልተኛ የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤት መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?
የቻርተር አስተዳደር ድርጅቶች ወይም CMOs በርካታ የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤቶችን የሚያስተዳድሩ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ተቋሞች ናቸው። እነሱ አብዛኛውን ጊዜ ወጪያቸውን ለመቀነስ ለህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤቶች የቢሮ የድጋፍ ሰጭ አገልግሎቶችን ያቀርባሉ፣ ነገር ግን ጥቂቶቹ ሰፋ ያለ የአገልግሎቶች ማእቀፎችን ይሰጣሉ። ገለልተኛ ወይም “ጀማሪ” የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤት ማለት በትምህርት ቤቱ ባለአደራ ቦርድ የሚካሄድ ማለት ነው።
ስለህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤቶች ስናወራ የሚሳተፉት ሌሎች የገንዘብ ድጋፍ ምንጮች ምንድን ናቸው?
የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤቶች ለትርፍ የተቋቋሙ ባለመሆናቸው፣ እነሱ የገንዘብ ድጋፍ የትምህርት ቤቱን ተልእኮ እና ግቦችን ከሚደግፉ፣ከበጎ አድራጎት ድርጅቶች መቀበል ይችላሉ፣ እና ለህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤቶች ብቻ ለሆነ የገንዘብ ድጋፍ ማመልከት ይችላሉ።
የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤት ምንድን ነው?
የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤቶች ፈጠራን ለመፍጠር ነጻ የሆኑ ገለልተኛ የሆኑ እና ለተማሪ አፈጻጸም ተጠያቂ የሆኑ የህዝብ ትምህርት ቤቶች ናቸው። እነሱ በህዝብ ገንዘብ የሚደገፉ፣ ከክፍያ ነጻ፣ እና ሃይማኖታዊ ያልሆኑ ናቸው። እንደባህላዊ የህዝብ ትምህርት ቤቶች፣ እነሱ ለሁሉም የ DC (ዲሲ) ኗሪዎች ክፍት ናቸው እና እንደተመዘገቡ ተማሪዎች ቁጥር የህዝብ ገንዘብ ያገኛሉ። የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤት ወጪዎቹ፣ አስተዳደሩን፣ የሰው ሀይሉ፣ እና የማስተማር ዘዴዎችን አስመልክቶ ሙሉ ስልጣን አለው።
የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤቶች ለቁሳቁሶች ከከተማው የገንዘብ ድጋፍ ያገኛሉ?
አዎ። የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤቶች በየአመቱ ለእያንዳንዱ ተማሪ ለቁሳቁሶች
$3,335 ይሰጣቸዋል። እያንዳንዱ የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤት በተማሪው የክፍል ደረጃ፣ የልዩ ትምህርት ሁኔታ እና ፍላጎቶች፣ እና ሌሎች ምክንያቶችን መሰረት ባደረገ መልኩ በእያንዳንዱ ተማሪ መደብ መሰረት ክፍያ ይቀበላል። የገንዘብ ድጋፍ በ DC (ዲሲ) መንስግስት ለትምህርት ቤቶቹ በየሩብ አመቱ በቀጥታ የሚሰጥ ነው፣ ከጁላ ይ ጁን 30 የበጀት አመት መሰረት ከጁላይ 15 ጀምሮ ክፍያ ይፈጸማል። እዚህ የበለጠ ይማሩ፣ https://dcpcsb.org/dc-public-charter-school-pupil-funding-analysis
የ DC ትምህርት ቤት ማሻሻያ ህግ ምንድን ነው?
የ DC ትምህርት ቤት ማሻሻያ ህግ፣ ወይም SRA ፣ ሪፈር የሚያደርገው በዲሲ ውስጥ ያሉ የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤቶችን ያቋቋመውን የ DC ኮድ§§ 38-1802 እና ተከታዮቹን ነው ። SRAን እዚህ ያንቡ።
በህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤቶች ሀይማኖታዊ ስርዓተ ትምህርት እንዲሰጥ ይፈቀዳል?
አይቻልም። ሁሉም የህዝብ ትምህርት ቤቶች፣ እንደ ቻርተር ትምህርት ቤትነታቸው ሀይማኖታዊ ትምህርትን በተመለከተ እንደ ባህላዊ የህዝብ ትምህርት ቤቶች አይነት ተመሳሳይ ህጋዊ መስፈርቶችን መከተል አለባቸው።
ሁሉም ትምህርት ቤቶች የእንግሊዘኛ ቋንቋ ተማሪዎችን (ELL) ፍላጎቶች እንዲያሟሉ ይጠበቃል።
አዎ፣ ሁሉም ትምህርት ቤቶች የእንግሊዘኛ ቋንቋ የሚማሩ ተማሪዎችን እንዲያገለግሉ ይጠበቃል።
እኔ የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤት እንዴት ላገኝ እቻላለሁ?
እያንዳንዱ የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤት በአመራሩ፣ ባህሉ፣ የማስተማር ፍልስፍናው፣ አቀራረቡ፣ እና ዘዴዎቹ የራሱ የሆነ ልዩ የሆነ ነገር አለው። ጥቂቶቹ በጣም የተዋቀረ ትምህርታዊ አካባቢዎችን ይጠቀማሉ፣ በሌላ በኩል ሌሎቹ በቋንቋ ጥልቀት፣ የተደባለቀ ትምህርት፣ Montessori ፣ የዳሰሳ ትምህርት፣ የአዋቂ ትምህርት ፕሮግራሞች፣ እና ሌሎች ላይ ትኩረት ያደርጋሉ። የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤት ለማግኘት፣ የ የትምህርት ቤት ገጽታ መሳሪያን ይጠቀሙ።
በ My School DC የማይሳተፉ ትምህርት ቤቶች ምንድን ናቸው?
ምንም አዋቂ ተማሪዎች በ My School DC ከመዋእለ ህጻናት- 12 የሆነው የህዝብ ትምህርት ቤት ሎተሪ ላይ አይሳተፉም። በመጪው አመት የማይሳተፉ ከመዋእለ ህጻናት - 12 ትምህርት ቤቶች እዚህ ሊገኙ ይችላሉ። ስለነዚህ ትምህርት ቤቶች ጥያቄ፣ እባክዎ ትምህርት ቤቱን በቀጥታ ያግኙ።
እኔ ለአካዳሚክ ስራ የምርምር ጥናት እያደረግኩ ነው። ከ DC (ዲሲ) የቻርተር ትምህርት ቤቶች ዳታ እንዴት መሰብሰብ እችላለሁ?
DC PCSB የሁሉንም የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤቶች የሚሸፍን መደበኛ የሆነ የስምምነት ፍቃድ የለውም። አንድን ትምህርት ቤት መሰረት ያደረገ ዳታ መልሶ ለማግኘት፣ እያንዳንዱን ትምህርት ቤት ማግኘት አለብዎ ወይም ምርምርዎን የኛ ክፍት የሆነ የዳታ ፖርታል ፣ OpenDC PCSB በመጠቀም ይጀምሩ።
የመዋእለ ህጻናት 3 እና የመዋእለ ህጻናት 4 የመጨረሻ የጊዜ ወሰን ስንት ነው?
በ My School DC ማመልከቻ ለሚያስገቡ ተማሪዎች፣ የመዋእለ ህጻናት 3 አመልካች ሴፕቴምበር 30 ላይ 3 አመት ሊሆን ይገባዋል። የመዋእለህጻናት 4 አመልካች ሴፕቴምበር 30 ላይ 4 አመት ሊሆን ይገባዋል። ለሁሉም እድሜዎች ፣የመጨረሻ የእድሜ ወሰን እንደየትምህርት ቤቱ ይለያያል። የመጨረሻ የእድሜዎችን ወሰን ለማየት፣ የ My School DC ድረገጽን እዚህ ሪፈር ያድርጉ። ትምህርት ቤቱ በ My School DC ተሳታፊ የማይሳተፍ ከሆነ፣ እባከዎ ለበለጠ መረጃ የትምህርት ቤቱን ድርገጽ ይጎብኙ።
በግዛቱ ትምህርት ቤቶች፣ እንደ DCPS ፣ እና የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤቶች መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?
በDC የህዝብ ትምህርት ቤቶች (DCPS) እንደሚመራው እንደ ባህላዊ ትምህርት ቤቶች፣ የህዝብ፣ ከክፍያ ነጻ፣ እና ለሁሉልም ክፍት ናቸው። የሚለያዩበት ነጥብ ማእከላዊ ስልጣን ነው — የ DC (ዲሲ) የህዝብ ትምህርት ቤቶች ቻንስለር — ባህላዊ የሆኑ ትምህርት ቤቶችን ያስተዳድራል። በአንጻሩ፣ የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤቶች በ DC (ዲሲ) የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤት ቦርድ (DC PCSB) ስምምነቶች መሰረት በጸደቁ፣ ለትርፍ ባልተቋቋሙ ቦርዶቹ የሚተዳደሩ ገለልተኛ ትምህርት ቤቶች ናቸው።
ሌላው ልዩነት፣ በትርጉም DCPS ትምህርት ቤቶች ጉርብትናን መሰረት ያደረጉ ናቸው። በአቅራቢያው የሚኖሩ ተማሪዎች የመግባት ዋስትናቸው የተረጋገጠ ነው፣ ሆኖም፣ የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤቶች ለሁሉም ክፍት የሆኑ በመላው ከተማ ውስጥ ያሉ ትምህርት ቤቶች ናቸው።
የተማሪ ሪከርዶቼን የት ማግኘት እችላለሁ?
የተማሪን ሪከርዶች በሁለት መንገዶች ማግኘት ይቻላል። ተማሪው የተማረበት ትምህርት ቤት ክፍት ሆኖ ከቆየ፣ ትምህርት ቤቱን በቀጥታ ያግኙ። ትምህርት ቤቱ ከተዘጋ፣ የተማሪ ሪከርዶችን ለመጠየቅ የ DC PCSB በ(202) 328-2660 ያግኙ።
በ DC ውስጥ የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤት መማር የሚችል ማነው?
የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤቶች ነጻ እና ለሁሉም የ DC (ዲሲ) ኗሪዎች ክፍት ናቸው። የ DC የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤቶች በህዝብ የገንዝብ ድጋፍ የሚደረግላቸው በመሆኑ፣ በከተማው ውስጥ የ DC ኗሪዎች ብቻ በከተማው ትምህርት ቤት መማር ይችላሉ።
የ DC የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤቶች ምን ያክል ብዝሃዊነት አላቸው?
DC PCSB የ DC ብቸኛ የቻርተር ፍቃድ ሰጪ እንደመሆኑ መጠን፣ ፍትሃዊነትን በማረጋገጥ እና ለሁሉም የ DC (ዲሲ) የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤቶች ተደራሽ የመሆን ጠንካራ ሪከርድ አለው። በአጠቃላይ፣ የ DC የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤቶች በክልሉ ካሉት ትምህርት ቤቶች ከአማካዩ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ፐርሰንቴጅ ያላቸው የእንግሊዘኛ ቁንቋ እና የአካል ጉድለት ያለባቸው ተማሪዎች ፣ እና ከፍ ያለ ፐርሰንት ያላቸው የአፍሪካን አሜሪካዊ ተማሪዎችን ያገለግላል። የበለጠ ለመማር የ ፍሬነገሮች እና ቁጥሮች ገጽን ይጎብኙ።
በተጨማሪ፣ የ DC PCSB የቻርተር ማመልከቻ ሂደት መስራች ቡድኖቹ ሁሉንም ተማሪዎች እንዴት እንደሚያገለግሉ እንዲያሳዩ ይጠይቃል — በተለይም ታሪካዊ ጉዳት የደረሰባቸው ቡድኖችን — ይህም ሁሉም ተማሪዎች ብቁ እንዲሆኑ ወደሚለው ግብ ለማደግ ነው።
የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለመማር ነጻ ነው?
አዎ፣ የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለመማር ነጻ ናቸው። እነሱ በህዝብ የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግላቸው እና ከክፍያ ነጻ ናቸው። የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤቶች በተመዘገቡ ተማሪዎች ቁጥር ልክ የገንዘብ ድጋፍ ያገኛሉ።
ለህዝብ አስተያየት ምስክርነቴን እንዴት ማቅረብ እችላለሁ?
ህዝቡ በታቀዱ ፖሊሲዎች፣ አዲስ የቻርተር ትምህርት ቤት ማመልከቻዎች፣ የ ቻርተር ስምምነቶች ለመለወጥ በሚቀርቡ ጥያቄዎች ላይ አስተያየት እንዲያቀርብ ይበረታታል። አስተያየቶችዎ መታየታቸውን እና መመርመራቸውን ለማረጋገጥ፣ “የትምህርት ቤቱን ስም” ይለዩ እና እባክዎ ከሚከተሉት ዘዴዎች አንዱን ይጠቀሙ (እባክዎ አንዱን ብቻ ይምረጡ)፣
-
የጽሁፍ አስተያየት ያስገቡ በ፣
-
ኢሜይል፣ public.comment@dcpcsb.org [እርስዎ በማሽን የሚሰጥ ምላሽ ይደርስዎታል። ይህ አስተያየትዎ እንደደረሰን ማረጋገጫ ነው።]
-
የፖስታ ደብዳቤ፣ የሚመለከተው። Public Comment, DC Public Charter School Board, 3333 14th Street NW, Suite 210, Washington, DC 20010
-
በእጅ የሚሰጥ/መልእክተኛ፣ አስተያየትዎን ከላይ ባለው ተመሳሳይ የፖስታ አድራሻ ይላኩ
-
-
በአካል ለመመስከር ይመዝገቡ በ public.comment@dcpcsb.org። እያንዳንዱ ምስክርነቱን የሚሰጥ ሰው የሱን/የሷን ምስክርነት ለመስጠት ሁለት ደቂቃዎች ይሰጣቸዋል።
ጠቃሚ፣ ሁሉም አስተያየቶች ለህዝብ የሚገኙ ናቸው። በኢሜይል፣ በፖስታ ደብዳሜ፣ ወይም በእጅ የተሰጠ/ የተላከ አስተያየቶች ክፍት በሆነው ገጽ ላይ የህዝብ አስተያየት የሚለውን አገናኝ በመጫን ማግኘት ይቻላል። እኛ በግል የሚለዩ መረጃን ሲያስገቡ አናሻሽልም። እባክዎ ህዝብ እንዲያውቀው የሚፈግሉትን መረጃ ብቻ ያስገቡ።
እኔ በህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤት እንዴት ልመዘገብ እችላለሁ? My School DC ምንድን ነው?
ለአብዛኛው የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤቶች፣ ምዝገባ የሚከናወነው በ My School DC አማካኝነት ነው።
My School DC በሁሉም ተሰታፊ የህዝብ ትምህርት ቤቶች የአዲስ ተማሪዎች ምደባን የሚወስን የተለመደ ሎተሪ ነው። ተሳታፊ ትምህርት ቤቶችን ለማየት ፣ ይጎብኙ My School DC ድረገጽ።
My School DC ተሳታፊ የሆኑ ከመዋእለህጻናት- 12 ያሉ የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤቶች፣ DCPS ከአካባቢ ውጪ የሆኑ ትምህርት ቤቶች፣ መዋእለህጻናት 3 እና መዋእለህጻናት 4 DCPS ፕሮግራሞች እና DCPS የተመረጡ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች (ከ9-12 ክፍሎች) ላይ ለማመልከት የኦንላይን የመተግበሪያ መሳሪያ ነው።
ወደ My School DC እንዴት ማመልከት እንደሚቻል ላሉ አዘውትረው የሚጠየቁ ጥያቄዎች እና መልሶች እና የመጨርሻ ቀኖችን ለማክበር፣ ይጎብኙ የ My School DC ድረገጽ።
የቻርተር ጥያቄ ምንድን ነው?
የቻርተር ጥያቄ ቻርተር የሚመሰረትበትን ቁልፍ መረጃ ይዘረዝራል። ለምሳሌ፣ ጥያቄው የታቀደው ትምህርታዊ ፕሮግራሞች፣ የተማሪ ውጤቶች እና መመዘኛዎች፣ የአስተዳደር መዋቅር፣ ፖሊሲዎች፣ እና ትምህርት ቤቱ መከተል ያለበት ህጋዊ ደምቦችን ያካትታል።
የቻርተር ጥያቄ ፍቃድ ለምን ይከለከላል?
የ DC የህዝብ ቻርተር የትምህርት ቤት ቦርድ ለአዲስ የቻርተር ጥያቄዎች በጣም ጥብቅ የሆነ የፍቃድ መስፈርት አለው። የኛ ግብ በግዛቱ ውስጥ ጥራት ያላቸውን ትምህርት ቤቶች ለቤተሰቦች ማቅረብ ነው። አንድ ቻርተር ፍቃድ እንዲያገኝ፣ በማመልከቻው ላይ የተዘረዘረውን ሁሉንም መመርያዎች ማሟላት አለበት። በተልእኮው እና በፍልስፍናው መካከል መጣጣም፣ ለትምህርት ቤቱ እና/ወይም ለልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚታይ አስፈላጊነት መኖር አለበት። ልዩ የህብረተሰቡ ክፍሎች የሚያካትት መሆን አለበት። መስራቹ ቡድን የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤትን ለማካሄድ ችሎታ ያለው መሆኑን እና እቅዱ ፍቃድ እንዲያገኝ የሚያስችለውን ሂደት እንደሚያከናውን በቂ የሆነ ማስረጃ በተጨማሪ ማቅረብ አለበት።
የትምርት ቤት ቻርተር ከተሰረዘ ወይም ደግሞ ካልታደሰ ምን ይሆናል?
የትምህርት ቤት ቻርተር ከተሰረዘ ወይም ካልታደሰ፣ የኛ ቁጥር አንድ ግባችን ተማሪዎች ሊማሩበት የሚችሉ ሌላ ትምህርት ቤት ማግኘታቸውን ማረጋገጥ ነው።
ትምህርት ቤት እንዴት እንደሚዘጋ ስለሂደቱ ለበለጠ መረጃ፣ ያግኙ Lenora Robinsion-Mills በ lmills@dcpcsb.org።
ትምህርት ቤት ቻርተር እንዴት ነው የሚያገኘው?
ትምህርት ቤት ቻርተር ለማግኘት የቻርተር ማመልከቻ ለ DC የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤት ቦርድ ማስገባት አለበት። የቻርተር ትምህርት ቤትን ስለመጀመር የበለጠ ይማሩ እዚህ እና ለጥያ ቄዎች ያግኙ applications@dcpcsb.org ።
ነባር ትምህርት ቤት የቻርተር ትምህርት ቤት ለመሆን ሀሳብ ማቅረብ ይችላል?
አዎ። ብቁ የሆነ አመልካች ማመልከቻውን በማስገባት ሀሳቡን ማቅረብ ይችላል (1) በ Columbia (ኮሎምቢያ) ግዛት ያለ የህዝብ ትምህርት ቤትን ወደ የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤት ለመቀየር፣ (2) ነባር የግል ወይም ገለልተኛ ትምህርት ቤትን ወደ ህዝብ የቻርተር ትምህርት ቤት ለመቀየር፣ ወይም (3) አዲስ የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤት ለመመስረት። ትምህርት ቤቶችን መቀየር ተጨማሪ መስፈርቶች አሏቸው በ D.C። ኮድ § 38-1802.01 የሚገኙ።
አንዳንድ የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤቶች ለምን ይዘጋሉ?
የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤት የሚዘጋበት ሶስት ዋና ምክንያቶች አሉ። የመጀመርያው ምክንያት ትምህርት ቤቱ የቻርተር ግቦቹን አላሳካም። ለምስሌ፣ የቻርተር ትምህርት ቤት የሚጠበቀውን የአካዳሚክ ስኬት ካላሳካ፣ በ በ1995 የ DC የትምህርት ቤት ማሻሻያ ህግ (SRA) ላይ የተቀመጠውን የቻርተር እድሳት መስፈርትን አያሟላም። ሁለተኛው ምክንያት ትምህርት ቤት ህጉን አያከብርም። ሶስተኛው ምክንያት በጀት በሚገባ አለማስተዳደርን ያካትታል። በትምህርት ቤት ማሻሻያ ህግ ወይም SRA፣ የ DC PCSB ቦርድ ትምህርት ቤቱ የበጀት አላግባብ ማስተዳደር ሁኔታ ላይ በተደጋጋሚ መሳተፉን ከወሰነ የትምህርት ቤቱን ቻረተር ሊሰርዝ ይችላል እና ትምህርት ቤቱ አግባብ ያለውን ህግ ከጣሰ የትምህርት ቤቱን ቻርተር ሊሰርዝ ይችላል።
የአንድ አመልካች ለትርፍ ያልተቋቋመ ሁኔታዎች ምንድን ናቸው?
የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤት በ DC ኮድ Columbia (ኮሎምቢያ) ግዛት ለትርፍ ያልተቋቋሙ ኮርፖሬሽን ህግ፣ አርእስት 29፣ ምእራፍ 4 መሰረት፣ ሙሉ ፍቃድ ለማግኘት ለትርፍ ያልተቋቋመ ኮርፖሬሽን ሆኖ መደራጀት አለበት። ነገር ግን፣ ሂደቱ ተጀምሮ ነገር ግን በማመልከቻ ማስገቢያ ቀን ካልተጠናቀቀ ቻርተሩ በቅድመሁኔታዎች ፍቃዲ ሊያገኝ ይችላል። በእንዲዚያ አይነት ሁኔታዎች፣ ማመልከቻው ሙሉ ፍቃድ ከማግኘቱ በፊት የአመልካቹ መካተት መሟላቱ ቅድመ ሁኔታ ነው።
የቻርተር መስፈርቶች ምንድን ናቸው?
ቻርተር የማግኛ መመርያዎች ለልምድ ላላቸው ፈጻሚዎች እና ለጀማሪ አመልካቾች የተለያዩ ናቸው። የልምድ ያላቸው ፈጻሚዎች እና የጀማሪ ቡድኖች መመርያዎች እዚህ ይገኛሉ። ልምድ ያለው ፈጻሚ ማመልከቻዎች የተረጋገጠ የአካዳሚክ ስኬት ሪከርድ ያለውን የአንድ ትምህርት ቤት ሞዴልን ኮፒ አድርጎ ለመስራት ፍላጎት ላላቸው ለቻርተር አስተዳደር ድርጅቶች (Charter Management Organizations, CMO) ወይም ለትምህርት አስተዳደር ድርጅቶች (Education Management Organizations, EMO) ነው።
የጀማሪ ማመልከቻዎች የታቀዱት የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤት መጀመር ለፈለጉ የአካባቢው መስራች ቡድኖች ነው። ማመልከቻው የታቀደው መስራቹ ሙሉ በሙሉ አዲስ የሆነ ወይም ከነባር ትምህርት ቤት፣ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት፣ CMO ፣ ወይም EMO ጋር በጋራ በመሆን አዲስ የሆነ የትምህርት ቤት ሞዴል ዲዛይን ለማድረግ እና ለመተግበር ችሎታ ያለው መሆኑን ለመመርመር ነው።
ለእነዚህ ሁለቱም መስራች ቡድኖች፣ ይህን ሂደት መከተል አለባቸው።
-
በ ቻርተር ማመልከቻ መመርያዎች መሰረት፣ የጽሁፍ ማመልከቻ ማስገባት።
-
አቅምን በሚፈትን ቃለመጠይቅ ላይ መሳተፍ።
-
እንደ አግባብነቱ፣ የፈጻሚው ነባር ትምህርት ቤት(ቶች) የቦታ ጉብኝት ማዘጋጀት።
-
የህዝብ ውይይት የህዝብ አስተያየት ለምስክርነት መቅረብ የሚችልበት።